ካኒባሊዝም
ካኒባሊዝም ማለት በአንድ የዶሮ እርባታ ውስጥ ባልታሰበ ሰአት ዶሮዎቹን እርስ በእርስ እንዲነካከሱ የሚያደርግ አመል ሲሆን በተጨማሪም እርስ በእርስ በቁም ስልቅጥ ተደራርጎ እስከመበላላት የሚያደርግ እና ይህ ሲከሰት ዶሮዎቹ ሰይጣን የገባባቸው እስኪመስል ድረስ ባህሪያቸውን አውሬ እና ቅብዝብዝ የሚያደርግ በየትኛውም ፋርም ውስጥ ሊከሰት የሚችል ለባለቤቱ ግራ የሚያጋባ ክስተት ነው።

የፖችፎስትሩም ኮኮክ ተዳቅለው በምርምር ዲዛይን የተደረጉት ለልቅ እርባታ ነው። ከፍተኛ የበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ዶሮዎች ናቸው። ሴቷ የኮኮክ ዶሮ በ 4 ወር ከ 15 ቀኗ እንቁላል መጣል ትጀምራለች እናም እስከ 4 ዓመት ድረስ እንቁላል መጣሏን ትቀጥላለች።
አዞላ የውሃ ውስጥ አነሰተኛ ቅጠል ያለው እፅዋት ሲሆን ለዶሮዎች እንደ ተስማሚ ተጨማሪ ምግብነት ያገለግላል። ዕፅዋቱ በፕሮቲን የበለፀገ ሲሆን ካልሺየም ፣ ፖታሽየም እና ሌሎች 5 አይነት ለጤናቸው ተስማሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዞል።